የአክሱም የግሪክ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ ጽህፈት ቤት „የግሪክ ቋንቋ እና የባህል መማሪያ ማዕከል“ መቋቋም

In other languages: ENGRBG

እ.ኤ.አ.1821 የግሪክ ታሪካዊ አብዮት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ ካለፉት ሁለት መቶ (200) ዓመታት ወዲህ የሚከበረውን የግሪክ ዓመታዊ ክብረ በዓልን በማስመልከት የአክሱም የግሪክ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ ጽህ/ቤት “የግሪክ ቋንቋና ባህል መማሪያ ማዕከል” በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ መጀመሩን ይገለጻል፡፡

ይህ የትምህርት መርሃ ግብር በግሪክ ውስጥ ለመስራት ወይም ለመማር ለሚሄዱት እንዲሁም የግሪክኛ ቋንቋ ተናጋሪ ላልሆኑ ኢትዮጵያውያን ፣ የውጭ ዜጎች እና የግሪክ ቋንቋ ፣ ታሪክ እና ባህል ማወቅ ለሚፈልጉ ሁሉ ነው ፡፡

እነዚህ የግሪክ ትምህርቶች ሙሉ በሙሉ ያለክፍያ የሚቀርቡ ሲሆን ስድስት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው የአክሱም የግሪክ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ ጽ/ቤት ውስጥ በየሳምንቱ ዘውትር ሐሙስ እና ቅዳሜ ከ11:00 እስከ 12:30 ከሰዓት በኋላ የሚካሄዱ ናቸው ፡፡

ትምህርቶቹ የሚጀምሩበትን ቀን ቀጥሎ ያስታውቃል፡፡

ለሥልጠና መርሃግብሩ ምዝገባ ማመልከቻዎች (የተጠናቀቀ ቅጽ) ወይም ማብራሪያዎች በ archbishop.aksum@gmail.com ኢሜል ላይ እስከ 07/07/2013 ድረስ ይላኩ ፡፡

እያንዳንዱን የትምህርት ደረጃ ላጠናቀቁ ሰልጣኞች በቅጣይ በግሪክ የትምህርት ሚኒስቴር እና የሃይማኖት ተቋማት ዕውቅና ለተሰጣቸው የግሪክ የምስክር ወረቀት ፈተናዎች ላይ የመሳተፍ ዕድል ይሰጣል ፡፡

ምንጭ- Ἱερά Μητρόπολις Ἀξώμης Αἰθιοπίας | Holy Archdiocese of Aksum Ethiopia | የአክስኩም ግሪክ ኦርቶዶክስ ሊቀጳጳስ

DONATE TO DOXOLOGIA INFONEWS

BANK: Eurobank Bulgaria AD (Postbank)

IBAN: BG46 BPBI 8898 4030 6876 01

or through PayPal